ዜና | Oduu | News
የወረዳ 06 አስተዳደር ካቢኔ በተለያዩ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ።

የልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 አስተዳደር የካቢኔ አባላት በመደበኛ ስብሰባቸው በተለያዩ ወቅታዊ የልማት ስራዎች፣ በአገልግሎት አሰጣጥ ማሻሻያዎችና በመልካም አስተዳደር ጉዳዮች ላይ በዝርዝር በመወያየት ለቀጣይ ስራዎች አቅጣጫ የሚያመላክቱ ውሳኔዎችን አሳልፈዋል።

image
image
image
image
ዜና | Oduu | News
የልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 6 ብልጽግና ፓርቲ ኢንስፔክሽንና ስነ ምግባር ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት የ2018 በጀት አመት የመጀመሪያው 6ወር ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ግምገማና የቀሪ 6 ወራት የተከለሰ ዕቅድ ኦሬንቴሽን አደረገ።

በመድረኩ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የወረዳው ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ዮዲት ሰለሞን እንደገለጹት የውስጠ ፓርቲ ስራዎች ለማጠናከር በየግዜዉ የሚሰጡ የኢንስፔክሽን ስነ ምግባር ኮሚሽን ግብር መልስ መነሻ ያደረጉ ስራዎች በትኩረት በመስራት አሰራር ከማስጠበቅ አንጻር ሚናው የላቀ እንደሆነ ጠቅሰዋል። የወረዳው ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት ወ/ሮ አይቼሽ አዲስ እንደገለጹት በ6 ወራት ዉስጥ ያከናወናቸውን በርካታ ተግባራት ከኮሚሽን ህብረት ኮሚቴና ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ በመቀናጀት ከተደራጀበት አላማ አንጻር በአፈጻጸም ደረጃ የተሻለ ቢሆንም አሁንም ግን ዉስንነቶች እንዳሉና በቀጣይ መታረም እንዳለባቸው ኃላፊዋ ጠቁመዋል። ጥያቄዎቹንና አስተያየቶች መነሻ በማድረግ የኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊዋ እንደገለጹት በየደረጃው የሚገኙ የፓርቲ አባላትና አመራሮች ጨምሮ ፓርቲው ባስቀመጠው የአሰራርና አደረጃጀት፣ መመሪያዎችን የመጠበቅና የማስጠበቅ ሙሉ ኃላፊ ነት እንዳለው የተገለጸ ሲሆን በመጨረሻም የስራ አቅጣጫ በማስቀመጥ ዉይይቱን አጠናቅቀዋል።

image
image
image
image
ዜና | Oduu | News
"ምቹ የስራ አካባቢን በመፍጠር እና የሰራተኛውን እውቀት በአግባቡ በመጠቀም የተያዙ የልማት ግቦችን ለማሳካት በትኩረት እየተሰራ ነው።"- ወ/ሮ ልዕልቲ ግደይ

የልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር ለሰራተኛውና ለተገልጋዮች ምቹ የስራ አካባቢ ለመፍጠር የሚያስችሉ ደረጃቸውን የጠበቁ የተለያዩ አገልግሎት መስጫ ቦታዎች ስራ አስጀመረ። በዚህ ማስጀመሪያ መርሀ ግብር ላይ የክ/ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ልዕልቲ ግደይ አጠቃላይ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን ከለውጡ ማግስት ጀምሮ ዘላቂ እና ጠንካራ ተቋም ለመገንባት በትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል። ወ/ሮ ልዕልቲ አክለው ምቹ የስራ አካባቢን በመፍጠር እና የሰራተኛውን እውቀት በአግባቡ በመጠቀም የተያዙ የልማት ግቦችን ለማሳካት በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል። አስተዳደሩ፤ በላቀ ትጋትና ቁርጠኝነት ህዝብን በታማኝነት ለማገልገል ዝግጁ መሆኑን ያነሱት ወ/ሮ ልዕልቲ ሰራተኞች ደግሞ በታማኝነትና በቅንነት ህዝቡን እንዲያገለግሉ ምቹ ሁኔታ የሚፈጥር መሆኑን አስረድተዋል። የመንግስት ሰራተኞችን የኑሮ ጫናን ለማቃለል በመንግስት በኩል የተለያዩ ተግባራት እያከናወነ ይገኛል ያሉት ዋና ስራ አስፈፃሚዋ በስራው አከባቢ ያለአንዳች እንግልት አገልግሎት ለመስጠት እንዲያስችሉ ሰራተኛው አስፈላጊ የሆኑ ነገሮች በቅረብ እንዲያገኝ ያስችላል ብለዋል። በዚህ መርሀ ግብር ላይ የአገልግሎት አሰጣጡን የበለጠ ለማሳለጥ የሚያስችሉ ደረጃቸውን የጠበቁ ቴክኖሎጅዎችን ስራ ማስጀመሩን ወ/ሮ ልእልቲ አያይዘው ገልፀዋል። በዛሬው ዕለት ደረጃውን የጠበቀ የስፖርት ማዕከል፣ ሱፐር ማርኬት፣ የህፃናት መጫዎቻ ስፍራ፣ የመጀመሪያ ህክምና አገልግሎት መስጫ ማዕከል፣ ቤተ-መጽሃፍት እና ሌሎችንም አገልግሎቶች ስራ አስጀምሯል። በተያያዘ አስተዳደሩ ስታንዳርዱን የጠበቀ የወረፋ ማስጠበቂያ፣ የውስጥና የውጭ ካሜራ መቆጣጠሪያ ሴንተር፣ ዲስፕሌዮች፣ ዲጅታል ዙም ሚቲንግ፣ QR ኮድ ያለው የሰራተኞች ባጅና ሌሎችንም የቴክኖሎጂ ውጤቶች ወደ ተግባር አስገብቷል።

image
image
image
image
ዜና | Oduu | News
የባለ ጉዳይ ቀን የአገልግሎት አሰጣጥ ምልከታ ተደረገ።

በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 አስተዳደር የዕለተ አርብ የባለጉዳይ ቀን የሴክተር ተቋማት አገልግሎት አሰጣጥ ምልከታ ተደርጓል። በምልከታው ጥቅል የየተቋማቱ የስራ ስምሪት እና የባለጉዳይ አያያዝ ታይቷል።

image
image
image
image
ዜና | Oduu | News
'ከጂኦ-ስትራቴጂያዊ ኩስመና ወደ ታደሰ ቁመና': የባህር በርና የብሔራዊ ጥቅም ጉዳዮች ውይይት ተደረገ።

በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 አስተዳደር የሚገኙ የመንግስት ሰራተኞች "ከጂኦ-ስትራቴጂያዊ ኩስመና ወደ ታደሰ ቁመና" በሚል ርዕስ በተዘጋጀ ሰነድ ላይ ወቅታዊ ሀገራዊና ዓለም አቀፍ አጀንዳዎችን በማንሳት ሰፊ ውይይት አካሂደዋል። ውይይቱ ሀገራዊ ስኬቶችን በመገንዘብ እና ብሔራዊ ጥቅምን በማስከበር ላይ ያተኮረ ነበር። የመድረኩ መክፈቻ ንግግር ያደረጉት የወረዳው የዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታና ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ዮዲት ሰሎሞን፣ ከለውጡ ማግስት ጀምሮ የሀገርን ከፍታ የሚያረጋግጡ በርካታ ስኬታማ ተግባራት ደረጃ በደረጃ እየተከናወኑ መሆኑን አንስተዋል። ሁሉም የመንግስት ሰራተኛ ይህንን ታሪካዊ ወቅት ተገንዝቦ የበኩሉን ድርሻ መወጣት እንዳለበት አሳስበዋል። ወ/ሮ ዮዲት አክለውም፣ በእድገት ጎዳና ላይ የምትገኘው ሀገራችን ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ላይ የተሰራውን ታሪክ፣ በባህር በር ጉዳይም ላይ መድገም እንደሚገባት አጽንኦት ሰጥተዋል። ይህንን ለማሳካት ሰራተኛው የስነ ልቦና የበላይነትን በመያዝ በብሔራዊ ጥቅም ላይ በጋራ መቆም እንዳለበት አስገንዝበዋል። የባህር በር ጉዳይ የህልውና ጉዳይ በመሆኑ በሰላማዊ መንገድ መልስ እንዲያገኝ እየተሰራ መሆኑን ገልጸው፣ የመንግስት ሰራተኛው በቁጭት በጋራ መቆም እንደሚገባ አሳስበዋል። በመድረኩ ለውይይት መነሻ ሆኖ የቀረበው ሰነድ በብሔራዊ ጥቅምና በጂኦ-ስትራቴጂያዊ ቁመና ላይ የሚያጠነጥን ሲሆን፣ ሀገራዊና ዓለም አቀፍ ጉዳዮችን ዳስሷል። ሰነዱን ያቀረቡት የወረዳው ፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ስንታየሁ ደበላ ናቸው። የውይይት መድረኩን የመሩት የልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 ም/ፓርቲ ኃላፊና የፖለቲካና አቅም ግንባታ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዳምጠው ወንታሞ ሲሆኑ፣ ባስተላለፉት መልዕክት፣ ሀገራዊ ስብራቶች በመጠገናቸው ኢትዮጵያ የማንሰራራት ዘመን ላይ እንደምትገኝ ገልጸዋል። አቶ ዳምጠው አክለውም፣ ትናንት አባቶቻችን ያስረከቡንን ታላቅ ሀገር ክብሯንና ታላቅነቷን በተጠበቀ መንገድ ለልጆቻችን እና ለሚመጣው ትውልድ ለማስረከብ በመንግስትና በህዝብ ርብርብ ወደ ቀደመ ሉዓላዊ ክብሯ እየተመለሰች መሆኑን አስገንዝበዋል። ውይይቱ ከተካሄደ በኋላ አስተያየት የሰጡ የመንግስት ሰራተኞች በበኩላቸው፣ እንደ መንግስት ሰራተኛ ውስጣዊ አንድነታችን በማጠናከር ጂኦ-ስትራቴጂያዊ ቁመናችን በመግናጸፍ ብሔራዊ ጥቅምን ለማስከበር በጋራ እንቆማለን ሲሉ ገልጸዋል።

image
image
image
image
ዜና | Oduu | News
የመጀመሪያ ሩብ አመት አገልግሎት አሰጣጥና ሪፎርም የሴክተሮች አፈፃፀም ላይ በመነሳት ስልጠናዊ ግምገማ ከስራ ሂደቶችና ከቡድን መሪዎች ጋር ተካሄደ፤

(ልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት፣ ጥቅምት 2018 ዓ.ም.) የልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ስንታየሁ ደበላ፣ ወረዳው በ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያው ሩብ ዓመት ባስመዘገበው የአገልግሎት አሰጣጥና ሪፎርም አፈጻጸም ላይ ያተኮረ ስልጠናዊ ግምገማ እና የመማክርት ጉባኤ ማካሄዱን አስታውቀዋል። አቶ ስንታየሁ እንደገለጹት፣ መድረኩ የተዘጋጀው በወረዳው የሚገኙ የሴክተር ጽ/ቤቶች የአንደኛ ሩብ ዓመት አፈፃፀማቸውን በመገምገም፣ የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችሉ የለውጥ አቅጣጫዎችን ለመቀየስ ነው። እያንዳንዱ የሥራ ዘርፍ (ሴክተር) በሩብ ዓመቱ ያከናወናቸው የአገልግሎት አሰጣጥ ሥራዎች፣ የሪፎርም ዕቅዶች አፈፃፀም፣ እና የህዝብ እርካታ ደረጃ ተገምግሟል። በመገምገሚያው ወቅት የተለዩ ጥንካሬዎችና ክፍተቶች ለሚመለከታቸው ቡድን መሪዎች በዝርዝር ቀርበዋል።

image
image
image
image
ዜና | Oduu | News
በልደታ ወረዳ 06 አስተዳደር የባለጉዳይ ቀን የአገልግሎት አሰጣጥ ምልከታ ተካሄደ።

በመልካም አስተዳደርና ግልጽነት መርህ መሠረት የዜጎችን አገልግሎት አሰጣጥ ለማረጋገጥ ያለመ የባለጉዳይ ቀን አገልግሎት አሰጣጥ ምልከታ አድርጓል። ምልከታው የተካሄደው በአስተዳደሩ ሥር የሚገኙ ሴክተር ተቋማት (ጽ/ቤቶች) በሚሰጡት አገልግሎት ጥራትና ቅልጥፍና ላይ ትኩረት ተሰጥቶ ነው። በምልከታው ሂደት በወረዳ አስተዳደሩ ሥር የሚገኙ የሴክተር ተቋማት ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ባለጉዳይን የሚያስተናግዱበት አግባብ ላይ ጥልቅ ቅኝት ተደርጓል።

image
image
image
image